📖በእግ/ር ተጠርታችኋል📖
         🌐Part 1

📖መጽሐፍ ቅዱስ ስናገር (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ. 1)


26፤ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።

27፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤

28፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥ይላል።

🚻ዛሬ አንድ ነገር ልነገራችሁ እፈልጋለሁ እናንተ በእግዚአብሔር ተጠርታችኋል።እናንተን የጠራችሁ ሰው አይደለም እግ/ር እራሱ ነው እንጅ።

🚻ወንድሞችና እህቶች መጠራታችሁን ተመልከቱ።እግ/ር ከእናንተ የሚበልጡ ብዙ ጠብባን፣ሀያላን፣ባላአባቶች ነበሩ ነገር ግን እነሱ አልተጠሩም እግ/ር የጠራን አንተንና አንችን እንጅ።

🚻እግ/ር የእራሱ አጀንዳ በእናንተ ለይ ልፈጽም ፈለገ። ይህን አጀንዳ መፈጸም ትችላላችሁ ተብለው የተመረጡት ጠብባን፣የዓለምን ዕውቀት ሁሉ የሚያውቁት፣ፈላስፈዎች፣astrologysit፣physicalsit፣biologsit፣..ወዘተ አይደሉሙ።ለዚህ አጀንዳ ብቁ፣ይመጥናሉ ናቸው ተብለን የተመረጥነው አንተና አንቺ ናቸው።

🚻ግን አንተና አንቺ የተመረጣችሁ ዕውቀትና ጥበብ ስላላችሁ አይደለም ግን ዕውቀትና ጥበብን የምሰጠውን ስላወቃችሁ፣ስለተከተላችሁ እንጅ። ምክንያቱም እግ/ር ዕውቀትንና ጥበብ ሰጭ ስለሆነ ነው።

📖መጽሐፍ ቅዱስ ስናገር " ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።" (የያዕቆብ መልእክት 1:5)ይላል።

🚻እግ/ር አንተንና አንቺን ለዚህ አጀንዳ አሁን አይደለም የመረጠው፣የጠራው አስቀድሞ ወደ ምድር ከመምጣታችሁ በፊት አስቀድሞ ወስኗል የወሰናቸውን እነዚይን ደግሞ ጠራቸው።

📖መጽሐፍ ቅዱስ ስናገር " አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 8:30)ይላል።

🚻ያንተና ያንች ጥር ከምድር ሳይሆን ከሰማይ ነወ።