እስቲ  ዛሬ ስለዚህ  ድንቅ  ኢትዮጲያዊ  እናውራ ተወልዶ  ያደገው በ  ባህርዳር  ከተማ  በ  ዎላ  ኪዳነ ምህረት ነው ፡፡ አፉን የፈታው በግዕዝ  ቋንቋ ሲሆን  በ 34 አመቱ  14 መፅሐፍ  የፃፈ  ድንቅ  ሰው   ነው ፡፡

edit

በጣም  እንዲታወቅ  ያደረገው  ዴርቶጋዳ  የተባለው መፅሀፉ  ሲሆን ÷ ዴርቶጋዳ  እና  ክቡር  ድንጋይ  የተባሉት መፅሀፎቹ ወደ እንግሊዘኛ  ተተርጉሞ ለንባብ  ቀርቧል ፡፡

edit

በባለፈው ስርዐት  ብዙ  ችግር  እንዳጋጠመው  ሚናገረው ይስማዕከ  የኦጋዴን  ድመቶች  በሚለው  መፅሐፉ  ቦታው  ድረስ  በመሔድ  ጥናት  በሚያደርግበት  ግዜ  ለ  እስር  ተዳርጓ  ነበር ፡፡  ያውም   ከአንበሳ ጋር ፡፡

edit

በመቀጠል መፅሀፉ  ታትሞ  ለገበያ ከቀረበ በኃላ  የመኪና  አደጋ  ደርሶበት  ብዙ  ተሰቃይቶ  ጀርመን  ሀገር  10  ሚሊየን ብር  ያስወጣ  ሕክምና  ካደረገ  በኃላ  አሁን  በሙሉ  ጤንነት  ላይ  ይገኛል ፡፡ አግብቶ  የፈታ  ሲሆን  የአንድ ወንድ  ልጅም  አባት  ነው ፡፡

edit

መፅሀፎቹ :-  ዴርቶጋዳ ÷ራማቶሓራ ÷ዣንቶዣራ÷  ዮራቶራድ÷ ዮቶድ÷ ተከርቸም÷ ተልሚድ÷ ክቡር ድንጋይ÷ የኦጋዴን ድመቶች ÷ደህንነቱ÷ ሜሎስ ÷የቀንድ አውጣ ኑሮ ÷የወንድ ምጥ    ናቸው

edit